የናታኒም እና የምህረት አገልግሎት

እንኳን ወደ ናታኒም እና ምህረት አገልግሎት በደህና መጡ

  1. የምሕረት አገልግሎት ምንነት

የምህረት አገልግሎት ቤተክርስቲያን ለአቅመ ደካሞች ፣ ለተገለሉ ወይም ለተቸገሩት እንክብካቤ እና ድጋፍ ለመስጠት የምታደርገውን የተደራጀ ጥረት ያመለክታል።

ይህም አቅመ ደካማ አዛውንቶችን ባልቴቶችን እና ወላጅ አልባ ህጻናትን ከመንከባከብ ጀምሮ ሁለንተናዊ  ድጋፍን እስከመስጠት ድረስ የተለያዩ ተግባራትን ያጠቃልላል። የምህረት አገልግሎት ማህበራዊ አገልግሎት ብቻ አይደለም; በተጨባጭ ደግነትና ርኅራኄ የክርስቶስን ፍቅር የሚያሳይ የወንጌል መግለጫ ነው።

ይህ አገልግሎት መጀመሪያ በቤተክርስቲያን በመቀጠልም በማኅበረሰቡ ውስጥ በጣም  ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች አካላዊ እና መንፈሳዊ ፍላጎቶችን ለማገልገል፣ የቤተ ክርስቲያንን የፍቅር እና ሌሎችን የማገልገል ተልእኮ የሚያንፀባርቅ ነው።

ራዕይ

የክርስቶስን ፍቅር እና ርህራሄ በማሳየት በቤተክርስቲያችን ውስጥ የለውጥ ሃይል መሆን፣ እያንዳንዱ አባል በደግነት እና በልግስና ተግባራት ውስጥ በንቃት እንዲሳተፍ ማበረታታት እና ምቹ እና ንጹህ የቤተክርስትያን አካባቢን መፍጠር።

ተልዕኮ

  1. ቤተክርስቲያናችንን ማጽዳት እና መንከባከብ፡ ንጹህ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ለአምልኮ የሚጋብዝ ቦታ መፍጠር።
  2. በበጎ አድራጎት ተግባራት መሳተፍ፡ በማህበረሰባችን ውስጥ ለተቸገሩት ድጋፍ መስጠት፡፡
  3. ህብረትን መገንባት፡- በቡድን አባላት መካከል እና ከማህበረሰቡ ጋር በትብብር የአገልግሎት ግንኙነቶችን ማጠናከር።

እሴቶች

  1. አገልግሎት፡ በድርጊታችን የክርስቶስን ፍቅር በማንጸባረቅ ሌሎችን እናገለግላለን።
  2. ታማኝነት፡- በሁሉም ተግባራችን ላይ ሀቀኝነትን እና ግልፅነትን እናከብራለን፣ ተግባራችን ከእምነታችን ጋር እንዲስማማ እናደርጋለን።
  3. ርህራሄ:- በዙሪያችን ያሉትን ሰዎች ፍላጎት ለመረዳት እና ለመረዳዳት እንተጋለን፡፡ በደግነት እና በርህራሄ እንመላለሳለን፡፡

የቡድኑ አላማዎች

  • የቤተክርስቲያንን አካባቢ ንጹህ ማድረግ፡- የቤተክርስቲያኗ የአምልኮ እና ህብረት ቦታ ንጹህ እና ምቹ ማድረግ።
  • ወገኖችን መደገፍ፡ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በመስራትና ግብአቶችን (resource) በማሰባሰብ አቅም ላጡና ለተቸገሩ ወገኖቻችን የአቅማችንን እርዳታ መስጠት።
  • ቤተሰብአዊነትን መገንባት፡- በቤተክርስቲያን እና በአካባቢው ማህበረሰብ ውስጥ መልካም ግንኙነቶችን መገንባት።

ቁጥራዊ መረጃዎች

አገልጋዮች

0

የህብረት ጽዳት ቀናት​

0

በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም የሚያደጉ ልጆች

0

የነጻ ስልጠና ተጠቃሚዎች

0

የወርሃዊ ነፃ ህክምና ተጠቃሚዎች

0

የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት ተጠቃሚዎች

0

ፎቶዎች

አመራሮች

አቶ ይትባረክ

የቡድኑ ሰብሳቢ

ወ/ሪ መክሊት

የቡድኑ ምክትል ሰብሳቢ

የአገልግሎት ክፍላችንን መቀላቀል ይፈልጋሉ ?

የናታኒም እና ምህረት አገልግሎት ክፍል አባልነት መሙያ ፎርም
Scroll to Top